አዲስ አበባና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች በቀጣዩ ሳምንት የሮቦቶች እግር ኳስ ውድድር ሊያካሂዱ ነው

የካቲት 17፣ 2009

አዲስ አበባና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች በቀጣዩ ሳምንት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የሮቦቶች እግር ኳስ ውድድር ሊያካሂዱ ነው።

ለጨዋታው  የሚያስፈልጉ  ሮበቶች  ከቻይና  ተገዝተው  ውድድሩ   በአዲስ አበባና  መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አማካኝነት የዲዛይን  ማስተካካያ   ተደርጎላቸው  ነው ሮቦቶቹ   ለእግር ኳስፍልሚያው ዝግጁ  የሆኑት።

ውድድሩን የሚያዘጋጀው አይኮግላብ ኢትዮጵያ  ዋና  ስራ አስፈፀሚ አቶ ጌትነት አሰፋ   ለኢቢሲ ኤፍ ኤም 97.1 እንዳሉት ዩኒቨርሲቲዎች እያንዳንዳቸው በሶስት  ሮበቶች ውድድሩን የሚያከናውኑ  ይሆናል።

ለግማሽ ሰዓት ያህል በሚካሄደው ጨዋታ  ግብ መቆጠር ካልተቻለ  የውድድሩ ፍፃሜ በፍፁም ቅጣት ምት የሚለይ ይሆናል።

በቀጣይም በአፍሪካ ደረጃ የሮቦት የእግር ኳስ  ውድድር ላይ ኢትዮጵያ እንደምትወከልም አዘጋጆቹ  ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ደረጃ ውድድሩን ባለፈው መስከረም ለማካሄድ  ታቅዶ የነበረ  ቢሆንም ሮቦቶቹን ወደ አገር ውስጥ የማስገባት ሂደቱ  በመዘግየቱ የካቲት 24፣2009 ለማካሄድ ቀን መቆረጡን  አዘጋጆቹ  የሳይንስና   ቴክኖሎጂ  ሚኒስቴርና አይኮ ግላብ ኢትዮጵያ  ተናግረዋል።      

ሪፖርተር፥ ሰለሞን ጫላ