ፖፕ ፍራንሲስ ደቡብ ሱዳንን ሊጎበኙ ነው

የካቲት 20፣ 2009

የሮማው ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ደቡብ ሱዳንን ሊጎበኙ ነው፡፡

የሊቀ ጳጳሱ የጉብኝት ዓላማ በእርስ በርስ ግጭት እና በድርቅ የሚሰቃዩት የደቡብ ሱዳን ዜጎች ትኩረት እንዲያገኙ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡

ፖፕ ፍራንሲስ ባለፈው ጥቅምት ወር የካቶሊክ እንዲሁም የሌሎች ቤተክርስቲያናት ቀሳውስት ደቡብ ሱዳንን እንዲጎበኙ ጥሪ አድርገውላቸው እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ከሌሎች ቤተክርስቲያናት ጋር በመተባበር ለደቡብ ሱዳን ሰላም እንዲሚሰሩም ገልፀዋል፡፡

የኘሬዝዳንት ሳልቫኬር መንግስት ባለፈው ሳምንት በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ረሃብ መከሰቱን ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ፡- ሮይተርስ