ፕሬዝዳንት ትራምፕ አዲስ የጉዞ እገዳ አፀደቁ

የካቲት 28፣ 2009

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከስድስት አገራት ወደ አሜሪካ በሚገቡ ተጓዦች ላይ አዲስ የጉዞ እገዳ ትዕዛዝ እንዲተላለፍ በፊርማቸው አጸደቁ፡፡

የአሸባሪዎችን ጥቃት ለመከላከልና የአገሪቱን ደህንነት ለማስጠበቅ በሚል ምክንያት እገዳ ከተጣለባቸው 6 አገራት ውስጥ ሦስቱ የአፍሪካ አገራት ናቸው

አዲሱ ዕገዳ ከ10 ቀናት በኋላ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡  

ፕሬዝዳንቱ ከዚህ ቀደም አፅድቀው ከነበረው የሰባት አገራት የስደተኞች የጉዞ እገዳ ውስጥ የአፍሪካዎቹ ሶማሊያ፣ ሊቢያና ሱዳን በድጋሚ የተካተቱ ሲሆን ኢራቅ ከአዲሱ እገዳ ውጭ ተደርጋለች፡፡

ኢራቅ እገዳው ከተጣለባቸው አገራት ዝርዝር ውጭ የተደረገችው የአገሪቱ መንግስት የቪዛ ስርአቱን በማጠናከሩ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ኢራን፣ የመን እና ሶሪያ ላይ የእገዳ ትዕዛዙ ከተላለፈባቸው 6 አገራት ውስጥ በድጋሚ ተካትተዋል፡፡

አዲሱ የእገዳ ትእዛዝ ፍቃድ የተሰጣቸውን ስደተኞች አይመለከትም ተብሏል፡፡

አዲሱን ትእዛዝ በውጭ ጉዳይ ሚስትሩ ሬክስ ቲሌረሰን፤ በዋና አቃቢ ህግ ጄፍ ሴስዮንስ እና የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ፀሃፊ ጆን ኬሊ በጋራ ይፋ ተደርጓል፡፡

የአሜሪካ ፌደራል ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም ውድቅ ያደረገው የእገዳ ትእዛዝ በአየር መንገዶች ከፍተኛ መደናገሮችን ፈጥሮና በተቃውሞ ሰልፎች ታጅቦ ማለፉ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ እና አፍሪካን ኒውስ