የዋጋ ግሽበቱ ወደ 7 በመቶ ከፍ አለ

የካቲት 28፣ 2009

የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ጥር ከነበረው 6 በመቶ የካቲት ወር ወደ 7 በመቶ ከፍ ማለቱን ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የምግብ ዋጋ ግሽበት ባለፈው ወር 5 በመቶ የነበረ ሲሆን፤ በየካቲት ወር ላይ ግን ወደ 7 ነጥብ 8 በመቶ ማሻቀቡን ታውቋል፡፡

በአንፃሩ ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች የዋጋ ግሽበት ጥር ላይ 7 ነጥብ 4 በመቶ የነበረ ሲሆን፤ በየካቲት ደግሞ ወደ 6 ነጥብ 2 በመቶ መቀነሱ ተመልክቷል፡፡