አቶኒዮ ጉቴሬዝ የሶማሊያን ሰብአዊ ቀውስ ትኩረት ለመስጠት ሞቃዲሾ ገቡ

የካቲት 28፣ 2009

የተባበሩት መንግስታት ድርጀት (ተ.መድ) ዋና ፀሃፊ አቶኒዮ ጉተሬዝ በሶማሊያ ያለውን የርሃብ እና የኮሌራ ችግር ትኩረት እንዲሰጠው ለማስቻል ዛሬ ሞቃዲሾ ገብተዋል፡፡

ጉተሬዝ ከአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ፋርማጆ ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡

እዚህ የተገኘሁት ለሶማሊያ ህዝብ ያለኝን አጋርነት ለማሳየት ነው ያሉት ጉተሬዝ ዓለም የሶማሊያን ሰብአዊ ቀውስ ለመፍታት መረባረብ አለበት ብለዋል፡፡

ጉቴሬዝ ጨምረውም በሀገሪቱ ብዙ አሳዛኝ ክስተቶች እየተስተዋሉ ቢሆንም በአዲሱ ፕሬዝዳንት የሚታይ ተስፋ እንዳለ ገልፀዋል፡፡

በሶማሊያ በተከሰተው ረሃብ እና ኮሌራ የእንስሳት እና የሰው ህይወት እየጠፋ መሆኑን ዘገባው ያስረዳል፡፡

አምስት ሚሊዮን የሶማሊያ ዜጎች የሚመገቡት በቂ ምግብ እንደሌለ ተ.መ.ድ አስፍሯል፡፡

ምንጭ፡-አፍሪካን ኒውስ