ሱዳን እና ሶማሊያ ዜጎቻቸው ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያፀደቁትን አዲስ ህግ አወገዙ

የካቲት 29 ፣ 2009

ሱዳን እና ሶማሊያ ዜጎቻቸው ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያፀደቁትን  አዲስ  ህግ አወገዙ፡፡

አሜሪካ  የሶማሊያ፣ሱዳን፣ የመን፣ ኢራን፣ ሊቢያ እና ሶሪያ  ዜጎች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ መከልከሏን አጥብቀው እንደሚቃወሙ ሱዳን እና ሶማሊያ አመልክተዋል፡፡

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ እንዳሉት በአሜሪካ የሚኖሩ  የሶማሊያ ዜጎች ያበረከቱትን አስተዋፅኦ ማሳየት ሲገባ ጥቂት ዜጎች ችግር መፍጠራቸው ምክንያት ሊሆን አይገባም ብለዋል፡፡

ሶማሊያ አሸባሪዎችን ለመዋጋት እየሰራች መሆኑም ከግምት ውስጥ  መግባት ነበረበትም  ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡

የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ የሱዳን ዜጎች በምንም ዓይነት የአሸባሪነት ተግባር ባልተሳተፉበት ሁኔታ ይህ እገዳ መምጣቱ አስነዋሪ ነው ብለዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ኢራን የአሜሪካ ተግባር ህገ ወጥ ነው ሰትል መግለጿም ይታወሳል፡፡

ክልከላው ከተደረገባቸው ስድስት ሀገራት ሶስቱ በመንግስት ድጋፍ አሸባሪዎች የሚፈልቁባቸው፣ ተጨማሪ ሶስቱ ደግሞ ጠንካራ መንግስት ባለመኖሩ የአሸባሪዎች መፈንጫ የሆኑ ናቸው ሲል የአሜሪካ መንግስት ገልጿል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ