ሰራዊታቸውን ወደ ሶማሊያ ለላኩ አገራት ድጋፍ እንዲደረግ የመንግስታቱ ድርጅት ጠየቀ

የካቲት 30፣ 2009

አልሻባብ በሶማሊያ የሚያደርሰውን ጥቃት ለመከላከል ሰራዊታቸውን ወደ ሀገሪቱ ለላኩ የአፍሪካ አገራት ድጋፍ እንዲደረግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ጠየቀ፡፡

አሚሶም በሶማሊያ ሽብርተኝነትን ለመከላከልና መረጋጋትን ለማስፈን በሚያደርገው ጥረት ዘላቂ ድጋፍ ያስፈልገዋል ያሉት የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉታሬዝ ናቸው፡፡

አሚሶም ከሚጠበቅበው በታች በቁሳቁስ የተደራጀ ነው ያሉት ጉታሬዝ በዚህ ውስጥም ቢሆን ግን ውጤታማ ስራ በማስመዝገብ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ጅቡቲና ብሩንዲ የተወጣጡ 22 ሺህ ወታደሮች በአሚሶም ጥላ ስር ሶማሊያ ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡

የአውሮፓ ህብረት አሚሶምን ለመደገፍ ቀዳሚ ሲሆን፤ በዓመት 200 ሚሊዮን ዶላር ለዚሁ ስራ ወጪ ቢያደርግም ድጋፉን በ20 በመቶ ቀንሶታል፡፡

እ.አ.አ ከ2007 ጀምሮ በሶማሊያ የተሰማራው የአሚሶም ጦር አልሻባብን ከሞቃዲሾና ከሌሎች ዋና ዋና ከተሞች አስለቅቋል፡፡

ምንጭ- ኤቢሲ ኒውስ