ለአፍሪካ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ወሳኝ ነው፡- ተመራማሪዎች

የካቲት 30፡2009

የአፍሪካን ግብርና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማገዝ ለዜጎቿ ዘላቂ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ዴይሊ ኔሽን ዘገበ፡፡

ከአፍሪካ አገራት የተውጣጡ የግብርና ባለሙያዎች አዲስ አበባ ተሰባስበው እየመከሩ ሲሆን የአህጉሪቱ የሰብል ምርት በእድሜ በገፉ ሰዎች እየተሰራ እንደሆነና አዲሱ ትውልድ ከግብርና ስራ ይልቅ ወደ ቢሮ ስራ እንደሚያተኩር ተመልክቷል፡፡

አዲሱ ትውልድ የአባቶቹን የግብርና ስራ ለማስቀጠል ካልቻለ ትውልድ ሲተካ ምርታማ መሬቶች ጾም የሚያድሩበት አደገኛ ሁኔታ እንዳለም ባለሙያዎቹ አስታውቀዋል፡፡

የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የጋራ ገበያ በባዮ ቴክኖሎጂና በባዮ ሴፍቲኔት ላይ ለመወያየት ባዘጋጀው መድረክ ከአፍሪካ አገራት የተውጣጡ ባለሙያዎችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡   

ግብርናን ለሁሉም የእድሜ ክልልና ፆታ ተስማሚ በማድረግ እንዲሁም በቴክኖሎጂ መደገፍ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡

ባዮ ቴክኖሎጂን መጠቀም እንደ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ኡጋንዳና ግብፅ ያሉ አገራት በተለይ በምግብ ደህንነት፣ በማህበራዊ ምጣኔ ሀብት እና በአካባቢ ደህንነት ላይ ባለው ተፅእኖ ሙሉ ለሙሉ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ ተመራማሪዎች ግን የተፈጥሮ ሀብት ጋር እንደማይገናኝ ይገልጻሉ፡፡

የግብርና ምርትን ለማሳደግ የምንጠቀማቸው የቴክሎሎጂ ግብአቶች ተፈጥሮ ደህንነት ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ እንደሚገባምተጠቁሟል፡፡

በተመራማሪዎችና በሚድዲያ በኩል መልካም ግንኙነት መፍጠር ባዮቴክኖሎጂን ከባዮሴፍቲ ጋር በማቀናጀት የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፈጠር ከፍተኛ ሚና እንዳላቸውም ተገልጿል፡፡