የቲማቲም እና የ የፍራፍሬ ምርቶች አቅርቦት በቅርቡ ይስተካከላል

የካቲት 30፣ 2009

ለቲማቲም እና ለአንዳንድ የፍራፍሬ ምርቶች አቅርቦት ማነስ ምክንያት የሆነው የአየር መዛባት ጊዜያዊ የነበረ በመሆኑ በቅርቡ የምርቶቹ አቅርቦት ይስተካከላል ተብሎ እንደሚጠበቅ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በበኩሉ በአየር ንብረት ምክንያት የተከሠተውን የአቅርቦት እጥረት ምክንያት በማድረግ ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ህገወጥ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡

 

በጌታቸው ባልቻ