በመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ

የካቲት 30፣ 2009

በመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉን የንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ባለፉት አራት ወራት በዓለም ገበያ የነዳጅ ምርቶች ላይ ተከታታይ የዋጋ ጭማሪ በመታየቱ በስራ ላይ ያለው የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን መከለስ አስፈልጓል።

በዚህም መሰረት የንግድ ሚኒስቴር ከመጋቢት 01 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ዋጋ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም በአዲስ አበባ፥ ቤንዚን በሊትር ብር 18.77፣ ነጭ ናፍታ በሊትር ብር 16.35፣ ነጭ ጋዝ በሊትር ብር 16.35፣ ቀላል ጥቁር ናፍታ በሊትር ብር 14.01፣ ከባድ ጥቁር ናፍታ በሊትር ብር 13.37 እና የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር ብር 16.07 ሆኗል።

ጭማሪው ከነገ መጋት 01 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 30 ቀን 2009 ዓ.ም በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል።

የሚኒስትሮች ምር ቤት መስከረም 2001 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በየወሩ እንዲከለስ ውሳኔ መስጠቱ ይታወሳል፡፡