የደቡብ ኮሪያው ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ከኃላፊነታቸው አገደ

መጋቢት 01 ፣ 2009

የደቡብ ኮርያዋ ፕሬዝዳንት ፓርክ  ጊዩን ሄይ ፍርድ ቤት ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የተደረሰውን ውሳኔ ማፅናቱን ተከትሎ ሙሉ ለሙሉ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ወሰነ፡፡

 

የደቡብ ኮሪያ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ዛሬ ባሳለፈው ውሳኔ በሙስና ቅሌት ተቃውሞ ቀርቦባቸው በጊዚያዊነት ከስልጣናቸው ታግደው የነበሩትን ፕሬዝዳንቷን ሙሉ ለሙሉ ከኃላፊነት ይወገዱ ብሏል፡፡

ፕሬዝዳንት ፓርክ ከስልጣናቸው  እንዲነሱ የተላለፈው ውሳኔ በአገሪቱ የዲሞክራሲ ታሪክ የስልጣን ጊዚያችወን ሳይጨርሱ ከኃላፊነት የተነሱ መሪ በመሆን የመጀመሪያ ያደርጋቸዋል ተብሏል፡፡

ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንቷ ከታላላቅ ኩባንያዎች ጋር የሙስና ቅሌት ወስጥ እጃቸው አለበት በሚል ውሳኔውን ያፀናባቸው  የአገሪቱን  የድሞክራሲ እና  ህገ ደንብ ላይ ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ አድረገዋል ብሏል፡፡

ከስልጣናቸው የተነሱት ፕሬዝዳንት ፓርክ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቀጣይ የክስ ሂደታቸው  የሚታይ ይሆናል፡፡

በፕሬዝዳንቷ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም የፓርክ ደጋፊዎች በሲኦል አደባባይ መውጣታቸውን  አልጀዚራ ዘግቧል

አሁን ላይ  ጠቅላይ ሚንስትር ናቸው  የፕሬዝዳንቷን ስልጣን ደርበው አገሪቱን እየመሩ ያሉት፡፡

ፐሬዝዳንቷ ከኃላፊነት  መነሳታቸውን ተከትሎ የደቡብ ኮሪያ የምርጫ ህግ በ60 ቀናት ውስጥ  አስቸኳይ ምርጫ እንዲካሄድ ያዛል ተብሏል፡፡