ደቡብ ክልልን መሰረት ያደረገው የይርጋለም የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የመሰረት ድንጋይ ተጣለ

መጋቢት 05፣2009

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የደቡብ ክልልን መሰረት አድርጎ ለሚሰራው የይርጋለም የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርኩ መገንባት የክልሉ አርሶ አደር የሚያመርተውን ምርት እሴት የተጨመረበት አድርጎ በማቅረብ ተጠቃሚነቱን የሚያጎላ ነው ብለዋል፡፡

የሲዳማና የይርጋለም አርሶአደሮች በዋነኛነት ቡና፣ አናናስ፣ አቮካዶ፣ እንሰትና የተለያዩ ፍራፍሬዎችን እንዲሁም ስጋን በግብዓትነት ለማቅረብ ምቹ የገበያ ሰንሰለትን ለመፍጠር የሚያስችል ነው።

የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ተቋም ዩኒዶ ዋና ዳይሬክተር ሊያ ንግ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ወደ ኢንዱስትሪ ልማት እያደረገችው ያለው ሽግግር የሃገሪቱን እድገት ለማፋጠን አይነተኛ እርምጃ ነው ብለዋል፡፡

በቅርቡ በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ እንዲሁም በትግራይ ክልል ሁመራ ከተሞች የመሰረት ድንጋይ መቀመጡ የሚታወስ ነው።

ሪፖርተር ፡‑ አበበ ባዩ