ኮማንድ ፖስቱ የተወሰኑ ክልከላዎችን አነሳ

መጋቢት 06፣2009

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከወጡ መመሪያዎች ላይ ከተቀመጡ ክልከላዎች የተወሰኑትን አነሳ፡፡

በመረሰተ ልማት፣በፋብሪካዎች እና መሰል ተቋማት አካባቢ ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ከተፈቀደለት ሰራተኛ በስተቀር ማንኛውም ሌላ ሰው እንዳይንቀሳቀስ እንዲሁም በዚሁ አካባቢ የተላለፈው የሰዓት እላፊ ዛሬ ይፋ በሆነው የአፈጻፀም መመሪያ ቁጥር 3 መሰረት ተሽሯል የሚለው ከክልከላዎቹ መካከል ይጠቀሳል፡፡

ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ማንኛውንም ሰው በቁጥጥር ስር ማዋል፣ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ብርበራ ማድረግ በሬዲዮ፣ቴሌቪዥን ፅሁፍ ፣ምስል፣በፎቶ ግራፍ፣ቲያትር እና በፊልም የሚተላለፉ መልእክቶችን ለመቆጣጠር እና ለመገደብ የወጣው እገዳም በአዲሱ መመሪያ ተሽሯል፡፡

የተዘረፉ ንብረቶችን ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በመፈተሽ ለባለቤቶቹ እንዲመለሱ ማድረግ የሚለውም በአደሱ መመያ ቁጥር 3 እንዲቀር የተደረገ ነው፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሬታሪያት እና የመከላከያ ሚንስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ በመግለጫቸው አብዛኞቹ ክልከላዎች እንዲነሱ የተደረገው በአሁኑ ጊዜ የአገሪቱ ሰላም ወደ ነበረበት የተረጋጋ ሁኔታ እየተመለሰ በመሆኑ ነው ብለዋል።

ሪፖርተር፡- ጥላሁን ካሳ