የሩሲያ ተመራማሪዎች የፀሃይ ሀይልን በሳተላይት ወደ ምድር ሊያስተላልፉ ነው

መጋቢት 6፡2009

የሩሲያ ተመራማሪዎች የፀሃይ ሀይልን በምህዋር ላይ ከሚገኙ ሳተላይቶቻቸው ወደ ምድር ሊያስተላልፉ መሆኑን የአገሪቱ የመንግስት ጠፈር ምርምር ተቋም ገለጸ፡፡

በአሁኑ ወቅት የሙከራ ጥናቱ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን የገለጸው ተቋሙ ጥናቱ ከፀሃይ ኦክስጅን አዮዲንን በጨረር መልክ ወደ ምድር ለማስተላልፍ የሚያስችል መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከ2020 በኃላ ወደ ሙከራ ስራ ይገባል ተብሎ የሚጠበቀው እቅዱ በምህዋር ላይ በሚገኙ ሳተላይት ላይ የሚገጠሙ እንደሚሆኑም ተገልጿል፡፡

የኦክስጅን አዮዲን ጨረር ከፀሃይ በቀጥታ የሚሳብ ሲሆን 1 ሺህ ሜጋ ዋት የሚሆን ሀይልን ወደ ጨረር እንደሚቀይር ተገልጿል፡፡

አዲሱ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ላዘር ኦፕቲካል አዳፕቲቭ ሲስተም (laser-optical adaptive system) በመጠቀም የኤሌክትሪክ ሀይልን ማመንጨት እንደሚያስችል የሩስያ የዜና አገልግሎት መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ፤ የሩስያ የዜና አገልግሎት