የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአገሪቱን የኢንዱስትሪ ሽግግር የሚደግፍ መሆኑን ተ.መ.ድ አስታወቀ

መጋቢት 6፡2009

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አገሪቱ ወደ ኢንዱስትሪ የምታደርገውን ሽግግር እንደሚደግፍ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢዱስትሪ ልማት ድርጅት /ዩኒዶ/ ዋና ዳይሪክተር ሊ ያንግ አስታወቁ፡፡

ዋና ዳይሪሬክተሩ ዛሬ አየር መንገዱን ሲጎበኙ እንደገለፁት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን እርስ በእርስና ከተቀረው የአለም ክፍል ጋር በማገናኘት የሚያበረክተው አስተዋፅኦ የላቀ ነው፡፡

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም በበኩላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ እ.ኤ.አ 2025 ለማሳካት ይዞት የነበረውን እቅድ ከ9 ዓመታት በፊት ቀደም ብሎ ማሳካቱን አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ወደ አገሪቱ እንዲመጣና ለተለያዩ የአገሪቱ የውጭ ንግድ ምርቶች የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለውም አቶ ተወልደ ተናግረዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር መብራህቱ መለስ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ኢትዮጵያ ወደ ኢንዱስትሪ የምታደርገውን ሽግግር ለማፋጠን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢዱስትሪ ልማት ድርጅት /ዩኒዶ/ ጋር እንደምትሰራ ገልፀዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ጌታቸው ባልቻ