የብሪታኒያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

መጋቢት 07፣2009

የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ቦሪስ ጆንሰን ትናንት ያልተጠበቀ ጉብኝት በሶማሊያ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያን፣ ኬኒያን፣ ሶማሊያን እና ኡጋንዳን ለመጎብኘት ወደ ቀጠናው መምጣታቸውን ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ከቀጠናው መሪዎች ጋር በፅጥታ እና ድርቅ ጉዳዮች እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡

ቦሪስ ጆንሰን በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡

በተመሳሳይ የጁቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡