ሴቶች ለታዳሽ ሃይል ሚናቸው ሊጎላ ይገባል፡- ባለሙያዎች

መጋቢት 07፣2009

ሴቶች ታዳሽ ሃይልን በስፋት ለመጠቀም በሚደረገው ጥረት ወሳኝ ሚና ሊኖራቸው እንደሚገባ የኬንያ የዘርፉ ባለሙያዎች ተናገሩ፡፡

በማገዶ የሚከናወነው የምግብ ስራ ሴቶችን ለከፍተኛ ወጪ እንዲያወጡ ከማድረግ በተጨማሪ ለተለያዩ የጤና ዕክሎች እየዳረጋቸው እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ዘመናዊዩን የታዳሽ ሃይል ለመጠቀም ሴቶች ግንባር ቀድም ሊሆኑ እንደሚገባ ነው ሺንዋ የዘገበው፡፡

ነገር ግን ሴቶች ይህን ሚና እንዲወጡ ያለባቸውን የአቅም እና የገንዘብ ችግር ሊቀረፍ ይግባል እንደ ዘገባው ገለፃ፡፡

ለዚህም የሴት ስራ ፈጣሪዎችን ማበረታታት እና ተጠቃሚ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ዘገባው ያስረዳል፡፡

በኬንያ ብቻ በየዓመቱ 2 ሺህ ዜጎች ማገዶ ቤት ውስጥ በመጠቀም ለህልፈት እንደሚዳረጉ ዘገባው ያስረዳል፡፡

ምንጭ፣ ሺንዋ