አንድ የአልሸባብ ከፍተኛ ኮማንደር በሞቃድሾ ተገደለ

መጋቢት 07 ፣2009

አንድ የአልሸባብ ከፍተኛ ኮማንደር በሞቃድሾ ተገደለ፡፡

ጃዕፈር ኩካይ የተባለው የሽብር ቡድኑ ኮማንደር የተገደለው ትላንት ሌሊት ነው፡፡

በዋና ከተማዋ ሞቃድሾ አቅራቢያ  በተደረገ ዘመቻ  ኮማንደሩ ሲገደል በተደበቀበት ቦታ የጦር መሳርያ አብሮት ተገኝቷል፡፡

በሞቃድሾ የሂልዋ ቀጠና አስተዳደር ባለስልጣናት  የሶማሊያ  የፀጥታ ኃይሎች ባካሄዱት ዘመቻ  ግለሰቡን  እንደተገደለ ለሽንዋ አረጋግጠዋል፡፡

ጃዕፈር ኩካይ የተባለው የአልሸባብ ኮማንደር  እጁን እንዲሰጥ ቢጠየቅም  አሻፈረኝ በማለቱ ነው በፀጥታ ኃይሎች  እርምጃው የተወሰደበት፡፡