በኦሮሚያና ሶማሌ አዋሳኝ ቀበሌዎች በተነሳ ግጭት ተጠያቂዎችን ለህግ እንደሚያቀርብ መንግስት ገለፀ

መጋቢት 07 ፣2009

በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች  አዋሳኝ ቀበሌዎች በተነሳ ግጭት ተጠያቂዎችን ለህግ እንደሚያቀርብ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከምክር ቤቱ አባት በተለያዩ ጉዳች ላይ  ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የሁለቱ ክልሎች በአዋሳኝ ቀቤለዎቻቸው ዙሪያ በተነሳ ግጭት እጃቸው ያለበት የሁለቱም ክልሎች ታጣቂ ሚሊሻዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በሁለቱ ህዝቦች መከካከል ለዘመነናት የቆየ አብሮነት እንጂ ጠላትነት የለም ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ፣ ለግል ፍላጎታቸው መጠቀሚያ በአዋሳኝ ቀበሌዎች ዙሪያ ችግር ሲፈጥሩ የቆዩቱን እነዚህ ወገኖች ለህግ ለማቅረብ መንግስት  እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ክልሎች በህዝበ ውሳኔ የቀደመ ችግሮቻቸውን የፈቱ ቢሆንም  አሁን የሚታዩት  እነዚህን ችግሮች ወዳልተፈለገ  መንገድ እንዳይሄዱ ክልሎቹ በጋራ ይሰራሉ ብለዋል ፡፡

አወዛጋቢ የሆኑ 26 ቀበሌዎች ጉዳይ ቢሆንም በህዝብ ውሳኔው ውጤት መሰረት መፍታት እንደሚገባ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግርዋል፡፡

መንግስት ስላደረገው የደመወዝ ማስተካከያ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ በቅርቡ የተወሰደው እርምጃ  በመንግስት ሰራተኛው ያለውን  የገቢ አለመመጣጠን ለማስተካከል የተደረገ የደመወዝ ማስተካያ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡በዚሁ መሰረት ለመምህራንም ሆነ ለሌላው የመንግስት ሰራተኛ ይህን ከግምት አስገብቶ የደመወስኬል ማስተካከያ ማድረጉን  ገልፀዋል፡፡

በዘላቂነት ግን የሲቪል ሰርቪስና የሰው  ሀብት ልማት ሚኒስቴር በሙከራ እየተገበረው ያለው ለእኩል ስራ እኩል ክፍያ  አሰራር ተግባራዊ ሲደረግ ወጥ የሆነ የክፍያና የአሰራር ስርዓት ችግሩን እንሚፈታው ታምኖበታል ብለዋል፡፡

በኢትዮ‑ ኤርትራ ግንኙነት ዙሪያ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ፣ኢትዮጵያ ቀደሞ በያዘችው አቋሟ የኤርትራ መንግስት  ከጠብ አጫሪነቱ ድርጊት መግፋቱን የሚቀጥል ከሆነ  ሉዓላዊነቷን ለማስከበር ለትንኮሳው ተመጣጣኝ እርምጃ በመውሰዷን ትገፋበታለች ብለዋል፡፡

ይሁንጂ የሁለቱ አገራት ህዝቦችን የግንኙነት ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት ኢትዮያ አዲስ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት አቅጣጫ ልትከተል እንደምትችል ከምክር ቤታቸው አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ በተለያዩ ፖለቲካዊ፣ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ከምክር ቤት አባላት ለተነሳለቸው ጥያቄ ምላሽ በመስጠት የመንግስታቸውን ያለፉት ስድስት ወራት አፈፃፀም አስረድተዋል፡፡

በሰዒድ አለሙ