ተጎጅዎችን በዘላቂነት ለመደገፍ የሚያስችል አደረጃጀት በከንቲባ ዲሪባ ኩማ መሪነት ተዋቅሯል

መጋቢት 07 ፣2009

በቆሸ በተባለው አካባቢ በደረሰው  አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የተለያዩ ድጋፎችን በዘላቂነት እና በጊዚያዊነት ለማቅረብ በከንቲባ ድሪባ ኩማ መሪነት ተወቅሮ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

ዜጎች በፍጥነት የሚቋቋሙበት ደራሽ እርዳታ የሚያቀርቡ ኮሚቴዎች ከከተማ እስከ ወረዳ ድረስ መደራጀታቸውን የመስተዳድሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ሃይሌ ፍሰሃ በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

አዲስ ዘመናዊ የቆሻሻ ማስወገጃ ማዕከል በ14 ሚሊዮን ዩሮ በሰንዳፋ ሲገነባ  መቆየቱን የገለጹት አቶ ሃይሌ ፣ አካባቢውን ምቹ የመኖሪያ ቦታ ለማድረግ እየተሰራ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

ቆሸ 36 ሄክታር ከደረቅ ቆሻሻ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል ፕሮጀክ ስራ መሆኑን ገልፀው፡  ከዚህ ውስጥ 26 ሄክታር የሚሆነው እየለማ እንደነበር ነው ስራ አስኪያጁ ያብራሩት፡፡

በቀሪ 10 ሄክታር  ቦታ ላይ የነበሩ ዜጎች  ለአደጋ የተጋለጡ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

በከተማዋ በቆሼም ሆነ ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ የወንዝ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎችን ከስጋት ነፃ ለማድርግ ስራዎች መጀመራቸውም ገልፀዋል፡፡

ቆሼ ለ47 ዓመታት ግልጋሎት የሰጠ የከተማዋ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ሆኖ አገልግሏል፡፡