ክልላዊ መንግስታትና ከተማ አስተዳደሮች በቆሼ በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ እያደረጉ ነው

መጋቢት 9፣ 2009

በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰው የቆሻሻ ክምር መደርምስ አደጋ ለተጎዱ ዜጎች የተለያዩ ክልላዊ መንግስታትና ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ እያደረጉ ነው፡፡

የደቡብ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 5 ሚሊዮን ብር፣ የአዳማ ከተማ አስተዳደር 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር፣ የሃረሪ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 5ዐ4 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

እንዲሁም ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ 1 ሚሊዮን ብር፣ የኦሮሚያ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ሰራተኞች 4ዐሺ 381 ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ድሪባ ኩማ በአደጋው የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት የከተማው አስተዳደር ከህዝብ ጋር  እየሰራ መሆኑን ገልፀው ተጎጂዎቹ የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ሪፖርተር፤ አባዲ ወይናይ