በኢትዮጵያ የወይን ምርት በፍጥነት እያደገ ነው-የደቡብ አፍሪካ ቴሌቪዥን

መጋቢት 9፣ 2009

በአውሮፓና በቻይና የወይን ምርት ፍላጎት ማደጉን ተከትሎ ኢትዮጵያ የወይን ምርቷን በፍጥነት እያሳደገች መሆኑን የደቡብ አፍሪካ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ የሚመረተው ወይን ጣዕም ተፈላጊ በመሆኑ አብዛኛዎቹ ተጠቃሚዎች ይፈልጉታል ይላል ኮርፖሬሽኑ፡፡

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ወይንን ጨምሮ የአተክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን በማስፋፋት ቀዳሚ አገር መሆኗን የገለጸው የኮርፖሬሽኑ ዘገባ ወይንን ወደ ውጭ በመላክ ከአፍሪካ ቀዳሚ ከሆነችው ደቡብ አፍሪካ ጋር ተወዳዳሪ መሆኗ የማይቀር ነው ብሏል፡፡

ኢትዮጵያ የተለያዩ የወይን ብራንድ እያመረተች ወደ ኤሲያ፣ አፍሪካና ሰሜን አሜሪካ ኤክስፖርት እንደምታደርግና መንግንስት በዘርፉ ለተሰማሩ ገበሬዎች ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የደቡብ አፍሪካው ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዘገባ ያስረዳል፡፡

ምንጭ፤ የደቡብ አፍሪካ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን