የፖለቲካ ፓርቲዎች ባለመስማማታቸው በተጨማሪ ለመወያየት ቀጠሮ ያዙ

መጋቢት 9፣ 2009

በገዢው ፓርቲ ኢህአዴግና በተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በሚደረገው ድርድር ማን ያከናውን በሚለው ሃሣብና መድረክ መሪ ተደራዳሪ መሆን በመፈለጉ ስምምነት ላይ አልተደረሰም፡፡ 

ኢህአዴግን ጨምሮ 22 አገር አቀፍ የፖለተካ ፓርቲዎች የአገሪቱን የፖለቲካ ምህዳር ማስፋትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን ማጠናከር አላማው ያደረገ ውይይት፣ ድርድርና ክርክር ደንብ ላይ ለ6ተኛ ጊዜ ተወያይተዋል፡፡

የውይይት፣ ድርድሩና ክርክሩ ተሳታፊዎች እናማን ይሁኑ፤ በእነ ማን ይመራ በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ከመድረክ በስተቀር ሁሉም ህጋዊ ተቃዋሚ የፓለቲካ ፖለተካ ፓርቲዎች የውይይት፣ የድርድሩና የክርክሩ አካል መሆን ይችላሉ የሚል ሀሳብ ቀርቧል፡፡

መድረክ በበኩሉ ብቻውን ተቃዋሚ የፖለተካ ፓርቲዎች በመወከል ከኢህአዴግ ጋር ለመደራደር እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡

ውይይቱ፣ ክርክሩና፣ ድርድሩ በእነ ማን ይመራ በሚለው ሀሳብ ላይ ከኢህአዴግ በስተቀር ሁሉም ተቃዋሚ ፖለተካ ፓርቲዎች በገለልተኛና ነጻ አደራዳሪ አካላት መካሄድ አለበት የሚል ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

በዚህም ፓርቲዎች በድርድርና ክርክሩ መሪ አካል ላይ ስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው በጉዳዩ ላይ መጋቢት 20 2009 ዓ.ም ለመወያየት ስምምነት ላይ በመድረስ ውይይታቸውን አጠናቀዋል፡፡

ሪፖርተር፣ ሙባሪክ መሀመድ