የተጎዱ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም መንግስት እየሰራ ነው፡- ም/ጠ/ሚ/ር ደመቀ መኮንን

መጋቢት 10፣ 2009

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቆሼ አካባቢ በደረሰው አደጋ የተጎዱ ወገኖችን በዘላቂነት በአጭር ጊዜ ለማቋቋም መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን ያጡትን ዜጎች በስፍራው ተገኝተው አፅናንተዋል።

በአደጋው ወቅት የአካባቢው ወጣቶች እና ነዋሪዎች ህይወት ለማዳንና ተጎጂዎችን ለመደገፍ ላደረጉት ስራ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በፌቨን ተሾመ