መከላከያ ሰራዊቱ የአለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ተልዕኮው እያደገ መሆኑ ተገለጸ

መጋቢት 11፣ 2009

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በአለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ተልእኮ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የመከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የመከላከያ ሰራዊት ከአገሪቱ አልፎ በሩዋንዳ ፤በቡሩንዲ፤ በሱማሊያ እና በደቡብ ሱዳን ሰላም በማስፈን ረገድ ከፍተኛ ድርሻውን እያበረከተ መሆኑን የኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ዮሃንስ ድንቃየሁ ገልጸዋል፡፡

በመከላከያ ሚኒስቴር በሰላም ማስከበር ዋና መምሪያ ሁርሶ ሰላም መስከበር እና ኮንቲንጀንት ዋና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለ3 ወራት ያሰለጠናቸውን በአብዬ እና ሱዳን የሚሰማሩ ከ1 ሺህ 700 በላይ 16ኛ ሞተራይዝድ የሃይል ሻለቃ አባላትን ማስመረቁ ተገልጿል፡፡

የተመረቁት የሰላም አስከባሪ አባላት ህዝባዊ ተቀባይነት የበለጠ እንዲጠናከር ከማድረግ ረገድ የራሳቸውን አሻራ ማሳረፍ እንደሚገባቸው ገልጸዋል ሚንስትር ዴኤታው አቶ ዮሃንስ፡፡

የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት የተሰጠውን የሰላም ማስከበር ሚና በመወጣት እንዲሁም ህዝባዊ ወገንተኝነቱን በማሳየት ላይ እንደሚገኝ  የመከላከያ ሰላም ማስከበር  ዋና መምሪያ ሃላፊ  ሌተነ ጄኔራል ብርሃኑ  ጁላ ተናግረዋል፡፡

ተመራቂ የመከላከያ የሰላም አስከባሪ አባላት  የተሰጣቸውን ግዳጅ  በአግባቡ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ምንጭ፣ የድሬዳዋ መንግስት ኮሙኒኬሽን