የበአል የእርድ ከብት፣ የበግ፣ የፍየልና የዶሮ ገበያ ደርቷል

ሚያዝያ 5፣ 2009

በአዲስ አበባ በተለያዩ ገበያዎች ተዘዋውረን እንደተመለከትነው ለፋሲካ በአል ለርድ የሚሆኑ እንስሳት በበቂ ሁኔታ ለገበያ መቅረባቸውን አስተውለናል፡፡

የዘንድሮ የበአል ገበያ ከገና በአል አንፃር መጠነኛ ጭማሪ ያሳየ ቢሆንም የመዲናይቱ ነዋሪዎች ለበአል የሚያስፈልጋቸውን እንደያቅማቸው ወጥተው መሸመት ጀምረዋል፡፡

ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የእርድ ከብት በብዛት የገባ ሲሆን ከ9 ሺህ ብር ጀምሮ ለገበያ ቀርቧል፡፡

በግ ከ1200 ጀምሮ ፍየል ደግሞ ከ1500 ብር ጀምሮ ለገበያ የቀረበ ሲሆን ዶሮም ከ180 ብር ጀምሮ በአዲስ አበባ ገበያዎች በመሸጥ ላይ ነው፡፡

በናትናኤል ፀጋዬ