ግብፅ ለዓለም ጤና ድርጅት ዋና ፀሀፊነት እጩ ሆነው ለቀረቡት ዶ/ር ቴድሮስ ድጋፏን ሰጠች

ግንቦት 7፣ 2009

ግብፅ የአለም ጤና ድርጅት ዋና ፀሀፊ ለመሆን በእጩነት የቀረቡት የቀድሞ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ እና የጤና ጥበቃ ሚንስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን እንደምትደግፍ አስታወቀች፡፡

ዶ/ር ቴዎድሮስ እ.አ.አ ግንቦት 23 ጄኔቫ ላይ ለሚጠብቃቸው ውድድር በግብፅ ለሁለት ቀናት የቆየ የምርጫ ቅስቀሳ አድርገዋል፡፡

በአለም መድረክ ላይ አፍሪካን ወክለው ለቀረቡት ዶ/ር ቴድሮስ ግብፅ ያላትን ድጋፍ በውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዲኤታዋ ሞሀመድ ኢድሪስ በኩል አረጋግጣለች፡፡

አፍሪካ በዓለም አቀፉ መድረክ ፍትሀዊ ውክልና እንዲኖራት ግብፅ በጄኔቫ ለሚገኘው የልኡካን ቡድኗ በውጭ ጉዳይ ሚንስትር በኩል ጥብቅ መልእክት አስተላልፋለች፡፡  

ምንጭ፡- ኢጅብትኢንዲፔንዳንት