ቻይና የአለማችን ግዙፉን ተንሳፋፊ የጸሃይ ሃይል ማመንጫ ገነባች

ግንቦት 20፣2009

ቻይና በባህር ላይ የሚንሳፈፍ የአለማችን ግዙፉን የጸሃይ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት ማጠናቀቋን ገለጸች፡፡

ሰን ግሮው ፓወር ሰፕላይ በተሰኘ የቻይና ኩባንያ የተገነባው የጸሃይ ሃይል ማመንጫ 40 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል፡፡

የጸሃይ ሃይል ማመንጫው ውሃ ላይ በመሆኑ ቦታን ከመቆጠብ ባሻገር የውሃ ትነትን የመቀነስ ሚናም እንዳለው ተገልጿል፡፡

ቻይና በአለማች በበካይ ጋዞች መጠን ከፍ ብሎ የሚታይባት አገር ናት፡፡

የተጠናቀቀው የጸሃይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ቻይና የታዳሽ ሃይልን ለመጠቀም የደረሰችው ውሳኔ አካል መሆኑ ተነግሯል፡፡

ምንጭ፤ ዘ ኢንዲፔንደንት