የደም ቅድመ ምርመራ በማድረግ ሺዎችን ከካንሰር መታደግ ይቻላል-ጥናት

ግንቦት 29፣2009

የደም ቅድመ ምርመራ በማድረግ ሺዎችን ከካንሰር መታደግ እንደሚቻል መቀመጫውን አሜሪካ ቺካጎ ያደረገው የካንሰር ጥናት ኢንስቲቲዩት ገለጸ᎓᎓

በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ህዋሳት በሚሞቱበት ጊዜ መረጃዎችን ወደ ደም ስር ስለሚያስተላልፉ የካንሰር እጢዎችም ይህን መረጃ ስለሚያገኙ  ለህክምናው ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ነው የተገለፀው᎓᎓

ከዚህ በፊት ምልክቶች ሲታዩ ለተለያዩ የካንሰር አይነቶች የሚደረገው የደም ምርመራ ለበሽታው የሚደረገውን ህክምና ቀላል እንደሚያደርገው ነው ሳይንቲስቶች የገለፁት᎓᎓

አጥኚዎች ተስፋ እንዳደረጉት ለካንሰር በሽታ የሚደረገው አሰልቺ ምርመራ ለተወሰነ ጊዜ ብቻ በሚሰጥ  ህክምና በመተካት  ካንሰርን ለማከም  ይረዳል᎓᎓

የደም ምርመራው የካንሰር እጢውን በመጀመሪያው የእድገት ደረጃው የሚለየው ከሆነ ህክምናውም ውጤታማ በማድረግ በየአመቱ በበሽታው የሚሞቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት መታደግ ይቻላል ነው የተባለው᎓᎓

ምንጭ:-ሮይተርስ