በባህረሰላጤው አገራት መካከል ያለው አለመግባበት በውይይት እንዲፈታ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ጠየቁ

ሰኔ 5፣2009

በኳታር እና በስድስቱ የባህረሰላጤ አገራት መካከል ያለው አለመግባበት በውይይት እንዲፈታ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጠየቁ፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ ሱልጣን ቢን ሳድ አልሙርኪ የተመራ የልኡካን ቡድን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታው በባህረሰላጤው አገራት መካከል ያለውን የወቅቱን የፖለቲካ ቀወስ ለጠቅላይ ሚንስትሩ አስረድተው ኢትዮጵያ ከኳታር ጎን እንድትቆም ጠይቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም በአገራቱ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት በውይይት እንዲፈታ ኢትዮጵያ ከፖሊሲዋ የመነጨ አቋም እንዳላት ገልፀዋል፡፡

በአገራቱ መካከል ባለው ልዩነት ላይ ኢትዮጵያ ገለልተኛ የሆነ አቋም እንዳላትም ጠቅላይ ሚንስትሩ  አስረድተዋል፡፡

ሪፖርተር:-እዮብ ሞገስ