ፎርብስ አምስት ኢትዮጵያዊ ቱጃሮችን ይፋ አደረገ

ሰኔ7፣2009

ታዋቂው የቢዝነስ መፅሔት የሆነው ፎርብስ ከ50 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ያላቸውን አምስት ኢትዮጵያዊ ባለሀብቶችን ይፋ አደረገ፡፡

ባለሀብቶቹ በግብርና ውጤቶች፣ በምግብ ምርት፣ በግንባታው ዘርፍ እና በንግድ የተሰማሩ ናቸው ተብሏል፡፡

የቅባት እህል በመላክ ንግድ ስራ ላይ የተሰማሩት አቶ በላይነህ ክንዴ በመፅሔቱ የመጀመሪያውን ስፍራ ይዘዋል፡፡ በላይነህ ክንዴ እስከ 60 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያገኝ ዘገባው ያስረዳል፡፡

 የአምቦ ውሃ ባለቤት እና በማአድን ፍለጋ ስራ የተሰማሩት አቶ ቴድሮስ አሸናፊ ደግሞ ሁለተኛው ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙ ባለሀብት ናቸው፡፡

የኢስት አፍሪካ ሆልዲንግ ባለቤትና በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው የሚሰሩት አቶ ብዙአየሁ  ታደለም በኢትዮጵያ ቱጃሮች ተርታ ተመድበዋል፡፡

የኬኬ ፒ ኤል ሲ ባለቤት አቶ ከተማ ከበደ  እና በግንባታው ዘርፍ የተሰማሩት አኪኮ ስዩም አምባየ በቱጃሮች ተርታ የተቀመጡ ናቸ፡፡

እነዚህ ባለሀብቶች በዓመት በኢትዮጵያ ብር ከ1 ቢሊዮን በላይ የሚያገኙ ናቸው፡፡