በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የፖሊዮ በሽታ ተቀሰቀሰ

ሰኔ7፤2009

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የፖሊዮ በሽታ ወረርሽኝ  መቀስቀሱ ተነገረ።

በአገሪቱ ሁለት ህጻናት በበሽታው መያዛቸው  ታውቋል።

የአለም ጤና ድርጅት በአካባቢው የሚሰጠው የክትባት ሽፋን አነስተኛ በመሆኑ በሽታው በፍጥነት እንዳይዛመት ስጋቱን ገልጿል።

በአገሪቱ የተቀሰቀሰው  የፖልዮ በሽታ  ከአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2012 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ  መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

የፖሊዮ በሽታ በዋነኝነት ህጻንነት የሚያጠቃ ሲሆን ዘላቂ አካል ጉዳተኝነት ሊያስከትል ይችላል።