ማዕከሉ እጽዋትን በመንከባከብ ሀገራዊ ፋይዳ እያበረከተ ነው

ሰኔ 8፤2009

ከአራት መቶ ሄክታር በላይ ይዞታ ላይ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ የሆኑ ብርቅዬና አገር በቀል የእጽዋት ዝሪያዎችን በማስፋፋት ላይ መሆኑን የጉለሌ እጽዋት ማእከል አስታወቀ፡፡

የማእከሉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ጌታሁን እንደገለጹት በተፈቀደለት 705 ሄክታር ይዞታ ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ ያቋቋሙት የእጽዋት ማእከል ነው፡፡

በከዚህም ውስጥ በ400 ሄክታር መሬት ላይ በአገር በቀልና ብርቅዬ የእጽዋት ዝሪያዎች የመተካት ስራ መሰራቱን አቶ ያሬድ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ይህ ማእከል ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸው ከፍተኛ የሆኑ ብርቅዬና አገር በቀል የእጽዋት ዝሪያዎችን የመጠበቅ፣የመንከባከብ፣የማስፋፋት ስራ በማከናወን ለትውልድ መተላለፍ እንዲችሉ ማድረግ እንደሆነ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ማእከሉ በ2002 ዓ.ም. ሲቋቋም 240 የሚጠጉ አገር በቀል የእጽዋት ዝሪያዎች መኖራቸውን የገለጹት አቶ ያሬድ ማእከሉ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች በደረገው የእጽዋት ማሰባሰብ በአሁን ሰአት ከ700 በላይ አገር በቀልና ብርቅዬ የእጽዋት ዝሪያዎች በማእከሉ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ማእከሉ በተለያየ ደረጃ ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት የተግበር ተኮር የሰነ ምህደር ሳይንስ ትምህርት ድጋፍ እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

እስከ አሁንም ከ10 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የስነ ምህዳር ሳይንስ ትምህርት ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡ የተለያዩ ሳይንሳዊ ጥናቶችን ለማድረግም ማዕከሉ ትልቅ ፋይዳ እየሰጠ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የጉለሌ እጽዋት ማእከል ለህብረተሰቡ የኤኮ ቱሪዝም አገልገሎት ይሰጣልም ብለዋል፡፡

ማዕከሉ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ህንጻዎችና የመሰረተ ልማቶች ማስፋፊያ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በድርቤ መገርሳ