አርሶ አደሮች ለመኸር እርሻ በቂ ዝግጅት አድርገዋል

ሰኔ 8-2009

ከሚያዚያ አጋማሽ  በኃላ በአብዛኛው የአገሪቷ አከባቢዎች የዝናቡ ስርጭት እየተስተካከለ በመምጣቱ የአርሶ አደሩ የመኸር እርሻ  እንቅስቃሴ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዲገኝ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተገለጸ፡፡

የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ሚኒስቴር የተፈጠረውን ምቹ የአየር ሁኔታ በመጠቀም ከ12 ሚሊዮን  ሄክታር በላይ  መሬት  በዘር ለመሸፈን ከ60 ሺ በላይ የልማት ጣብያ ሰራተኞችን አሰማርቶ ለአርሶ አደሮች  ድጋፍና ክትትል እያደረጉ  ነው፡፡

አርሶ አደሮቹ የምርት ማሳደግያ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀሙ በባለሙያዎቹ ድጋፍና ክትትል ቢደረግላቸውም የማዳበሪያ አቅርቦቱ በቂ አለመሆኑ እንዳሳሰባቸው ይናገራሉ፡፡

ድጋፍና ክትትሉ አርሶ አደሩ ደጋግሞ በማረስ ፣በማረም ፣ፀረ ተባይ  መድሃኒቶችና ግብአቶች በመጠቀም በ2009 /2010 የታቀደውን 345 ሚሊዮን  ኩንታል ምርት በማሳካት  ላይ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ግብርናው ባለፈው አመት ለተመዘገበው የ8 በመቶ ምጣኔ ሀብታዊ እድገት የ2 ነጥብ 3 በመቶ አስተዋጽኦ እንደነበረው ተገልጿል፡፡

በቀጣይ ወደ ኢንዱስትሪ  ለሚደረገው ሽግግር  በመደገፍ በኩልም  ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል፡፡

በደረጄ ጥላሁን