በኢትዮጵያ ሶማሌ የሴቶችን ተጠቃሚነት እየጎለበተ ነው - የሴቶች ኮከስ

ሰኔ 8፤2009

በኢትዮጵያ ሶማሌ  ክልል የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እየተከናወነ ያለው ተግባር በአርአያነት የሚጠቀስ መሆኑን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ኮከስ አባላት ገለፁ᎓᎓

የምክር ቤቱ አባላት በክልሉ ባደረጉት የመስክ ምልከታ ሴቶች በተለያየ ደረጃ ባሉ ምክር ቤቶችና በውሳኔ ሰጭነት ቦታዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ የገመገመ ሲሆን በክልሉ ይደርስ የነበረውን የሃይል ጥቃት ለማስቀረት እየተሰራ ያለውን ስራ በመስክ ጉብኝት ገምግሟል᎓᎓

በዚህም በክልሉ እየተሰራ ያለው ስራ የሚያበረታታ መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ኮከስ አባላት ገልፀዋል᎓᎓

በአካባቢው ለድርቅ በተጋለጡ አካባቢዎች ድርቅን ለመቋቋም የሚያስችሉ የእንስሳት መኖ በማልማት ላይ የተሰማሩ ሴቶችም ስራው ተጠቃሚነታቸውን ከማረጋገጥ አንፃር ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል᎓᎓

በአካባቢው ባሉ መስራት በሚቻልባቸው ዘርፎች ላሉ ሴቶች እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴም አበረታች መሆኑንና ይህ አርአያነት ያለው ስራም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ኮከስ አባላት አሳስበዋል᎓᎓