የጃፓን ባለሃብቶች በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ መስራት ይፈልጋሉ

ሰኔ 8፤2009

የጃፓን ባለሃብቶች በቦሌ ለሚ ቁጥር 2 ኢንዱስትሪያ ፓርክ ውስጥ የኢንቨስትመንት ስራ መስራት እንደሚፈልጉ አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ የጃፓን የውጪ ንግድ ልኡካንን በጽ/ቤታቸው ባነጋገሩበት ወቅት የልኡኩ ምክትል ፐሬዝዳንት ካሉሚ ሄራኖ እንዳሉት ጃፓን በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ተጠቅማ በሀገሪቱ ላይ በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት ለማድረግ ትፈልጋለች፡፡

እንደ ሞጆ ደረቅ ወደብና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉ አማራጮች ምርቶቻቸውን በቀለሉ ለማጓጓዝ ምቹ ሁኔታን ስለሚፈጥሩ ወደ ኢንቨስትመንት እንዲቀላቁ መነሳሳትን እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ባለሃብቶቹ በቦሌ ለሚ ቁጥር 2 ኢንደስትሪያል ፓርክ ውስጥ ስራ መስራት እንደሚፈልጉና ኢትዮጵያ የምታመርተውን አበባ ወደ ሀገራቸው ለማስገባት መስማማታቸውንም ገልጸዋል፡፡

በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የቢዝነስ ዲፕሎማሲ ዳይሬክቶት ጀኔራል ወይዘሮ እየሩሳሌም አምደማሪያ የጃፓን ባለሃብቶች አሁን ኢንቨስት ከሚያደርጉባቸው ዘርፎች በተጨማሪ በሌሎች ዘርፎች እንዲሰማሩና ኢትዮጵያም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ መግለጻቸውን አስታውቀዋል፡፡

በሜሮን በረዳ