ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለሱ ሂደት ወሳኝ ደረጃ ላይ ደርሷል

ሰኔ 8፤2009

ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለሱ ሂደት ወደ ወሳኝ ምዕራፍ የተሻገረና የህብረተሰቡን ድጋፍ የሚሻ መሆኑን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የስደተኞች ቀንን እንድታስተናግድ መመረጧንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባወጣው ሳምንታዊ መግለጫው አስታውቋል፡፡