የተለያዩ ተቋማት የ8 ሚሊየን ብር የህዳሴ ቶምቦላ ገዙ

ሰኔ 9፣2009

ከ250 በላይ የሚሆኑ የፌደራል ተቋማት ሰራተኞች የ8 ሚሊዮን ብር የህዳሴ ግድብ ቶቦላ ሎተሪ መግዛታቸውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ጽሕፈት ቤቱ  ያዘጋጀው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቶምቦላ ሎተሪ ነገ ይወጣል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች የ2 ሚሊዮን ብር ሎተሪ ገዝተዋል፡፡ የሜቴክ ሰራተኞች በበኩላቸው የ6 መቶ ሺህ ብር ሎተሪ መቁረጣቸው ተገልጿል፡፡

አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ እና ኢትዮ ቴሌኮምም በተመሳሳይ እያንዳንዳቸው ከ3 መቶ ሺህ ብር በላይ የሎተሪ ግዥ ፈፅመዋል ተብሏል፡፡

ከግል ተቋማት ደግሞ ብርሃን ባንክ እና ዛብሎን ትሬዲግ እያዳንዳቸው ከ2 መቶ ሺህ ብር በላይ በማውጣት ሎተሪውን መግዛታቸው ታውቋል፡፡

በሎተሪው የቀረቡት ሽልማቶች እስከ 25 ሚሊዮን ብር የወጣባቸው ናቸው ተብሏል፡፡ ጽሕፈት ቤቱ በሎተሪ ሽያጩ እስከ 100 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ በዕቅድ ይዟል፡፡

የሎተሪው ገበያ ላይ መዋል የቦንድ ግዥውን እና ህዝባዊ ተሳትፎውን እንዳሳደገው ተገልጿል፡፡

ሎተሪው ነገ 11:30 ለባለዕድለኞች ይወጣል፡፡

በአዝመራው ሞሴ