የፀጥታው ምክር ቤት በዳርፉር ያለውን የሰላም አስከባሪ ሃይል ሊቀንስ ነው

ሰኔ 12፤2009

የተባበሩት  መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በዳርፉር ከተሰማራው የሰላም አስከባሪ ሃይል ቁጥሩን ለመቀነስ ማቀዱን ይፋ አድርጓል፡፡

የሰላም አስከባሪ ሃይሉ ይቀነስባቸዋል ከተባሉት ክፍሎች ውስጥ ደግሞ የፖሊስ ሃይል፤ የወታደር፤ የማጓጓዣና አስተዳደርን ይመለከታል ነው የተባለው፡፡

ይህ ውሳኔ ደግሞ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዳርፉራውያንን ህይወት አደጋ ላይ ይጥለዋል ነው የተባለው᎓᎓ በጦሩ ድጋፍ የሚከናወነውን የሰብአዊ ድጋፍ ለማካሄድ ትልቅ እንቅፋት ይፈጥራል የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡

በግዛቱ በተፈጠረው ግጭት 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ዳርፉራውያን ከቀያቸው ተፈናቅለው ወደ ቤታቸው መመለስ አልቻሉም᎓᎓

ካርቱም በበኩሏ የተመድን ውሳኔ ታላቅ ስህተት በማለት አጣጥላዋለች᎓᎓ በውሸት መረጃ የተመሰረተ

 ውሳኔ በማለት ቅሬታዋን አቅርባለች᎓᎓