ደረጃዎች ኤጀንሲ ለቴክኖሎጂና ጥራት ሽግግር ትኩረት መስጠት አለበት- ቋሚ ኮሚቴው

ሰኔ 10፤2009

ለቴክኖሎጂ ሽግግር ምቹ ሁኔታን በመፍጠርና የጥራት ተቋማትን አቅም በማሳደግ ጥራትን ማረጋገጥ እንዳለበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲን የ2010 በጀት እቅድ ላይ በተወያየበት ወቅት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳለው መኮንን በሀገር በቀል ምርቶችና አገልግሎቶች ደረጃዎችን በማዘጋጀት አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ማድርግ የበጀት አመቱ ዋና አላማ ነው ብለዋል፡፡

ኤጀንሲው 1ሺህ 326 የጥራት ደረጃዎችን ለንሄራዊ ደረጃዎች ካውንስል አቅርቦ እንዲያጸድቅ፤ የኢትዮጵያን ደረጃዎች ከአለም አቀፉ ደረጃዎች ጋር ማጣጣም እንዲሁም በስነምግባርእና ክህሎት የዳበረ ሰራዊት ማፍራት የሚሉትን በእቅዱ አካቶ ሊሰራ ይገባል ብሏል ቋሚ ኮሚቴው፡፡

ምንጭ፡ ተወካዮች ምክር ቤት