የአለም ስደተኞች ቀን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ይከበራል

ሰኔ 10፤2009

ሀገሪቱ ስደተኞችን በመቀበል እያስተናገደች በመሆኗ እለቱ በኢትዮጵያ እንዲከበር ተመራጭ እንዳደረጋት የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር አስታውቋል፡፡

የአስተዳደሩ ምክትል ምክትል ዳይሬክተር አቶ ዜይኑ ጀማል እንደገለጹት የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ለስደተኞች እዩሰጡ ያሉትን ድጋፍና እንክብካቤ እውቅና ለመስጠት ታስቦ ቀኑ በኢትዮጵያ እንዱከበር ተደርጓል፡፡

ቀኑም አጋርነት ለስደተኛ ወገኖቻችን በሚል መሪህ ቃል በጋምቤላ ክልል በጉኜሌ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ይከበራል ብለዋል፡፡

ቀኑ በኢትዮጵያ እንዲከበር መደረጉ ለስደተኞች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እና ለሀገሪቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተቀባይነት ለማጉላት እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፍሊፖ ገራኒን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ልኡካን የስድተኞች ቀን በሚከበርበት ጋምቤላ ክልል እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡