የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ቶምቦላ ሎቶሪ ዕጣ ወጣ

ሰኔ 11፤2009

ገቢው ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውለው የቶምቦላ ሎቶሪ አንደኛ ዕጣ ቁጥር 44 39 130 ሆኖ ወጣ።

ዕጣው የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ትናንት ማምሻውን በብሔራዊ ሎቶሪ አዳራሽ ወጥቷል።

በወጣው ዕጣ መሠረት አንደኛው ዕጣ ባለ ሦስት መኝታ ዘመናዊ አፓርታማ ቤት ያሸልማል።

ሁለተኛው የ2016 ስሪት ኃይሉክስ ደብል ጋቢና ተሽከርካሪ የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር ደግሞ 38 13 193 በመሆን ሲወጣ፤ ሦስተኛውና ባለ ሁለት መኝታ ዘመናዊ አፓርታማ ቤት የሚያስሸልመው ዕጣ ቁጥር 48 52 944 ሆኗል።

አራተኛውና አንድ ሊዮንቺኖ የማቀዘቀዣ የጭነት መኪና የሚያስገኘው ቁጥር 20 41 261 ሆኖ ሲወጣ፤ አምስተኛውና ባለ 40 የፈረስ ጉልበት የእርሻ ትራክተር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር ደግሞ 27 88 134 ሆኗል።

ሌሎችም ባለ ሦስት እግር ሞተር ባጃጆች፣ ማቀዘቀዣዎች፣ የውሃ ማጣሪያዎች፣ ላፕቶፖች፣ 32 ኢንች ኤል ኢዲ ቴሌቪዥኖች፣ ኤስ ፎር ሳምሰንግ ስማርት የሞባይል ስልክ ቀፎዎች  በዕጣው ተካተዋል። 

የማስተዛዘኛ ቁጥር ደግሞ ሦስት ሆኖ መውጣቱን ኢዜአ ዘግቧል።

የቶምቦላ ሎተሪው ከሚያዝያ አንድ ጀምሮ ሲሸጥ የነበረ ሲሆን፣ ከሽያጩም ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተግኝቷል።