ለኢትዮጵያ በተደራጀ መንገድ ድጋፍ እናበረክታለን- ዲያስፖራው

ሰኔ 12፤2009

ለኢትዮጵያ በተደራጀ መንገድ ድጋፍ እንደሚያበረክቱ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገለፁ᎓᎓

ከሃያ የተለያዩ ግዛቶች የተውጣጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን  የህዳሴው ምክር ቤት ተወካዮቸ  ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በተዘጋጀው የምክክር መድረክ

ላይ ተሳትፈዋል᎓᎓

የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳይገድበን በኢትዮጵያ የህዳሴ ጉዞ ላይ የራሳችንን ድርሻ ለመወጣት የህዳሴው ምክር ቤት ጥሩ ድልድል ሁኖናል ብለዋል  በምክክር መድረኩ ላይ ያገኘናቸው ተሳታፊዎች᎓᎓

አላማው በዚህ ምክር ቤት አማካኝነት ልማት ወደ ሃገር ቤት የሚገባበትን መንገድ መፍጠር ነው በማለትም ገልጸዋል᎓᎓

ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የዲያስፖራ ተሳትፎ ዘርፍ ሃላፊ  አቶ መርከቡ በየነ የምክክር መድረኩ በቀጣይ የበለጠ ተደጋግፈን ስንሰራ ምን ላይ ትኩረት ሰጥተን ስንሰራ የተሻለ ዲያስፖራውን ተደራሽ ማድረግ እንችላለን ብለዋል