ቀላል የማይባል የህብረተሰብ ክፍል የአደገኛ መድሃኒቶችና እጾች ሱስ ተጠቂ እየሆነ መምጣቱ ተገለፀ

ሰኔ 23፣2009

በአሁኑ ወቅት ቀለቀል የማይባል የህብረተሰብ ክፍል የአደገኛ መድሃኒቶችና እጾች  ሱስ ተጠቂ እየሆነ መምጣቱን የኢትዮጵያ የምግብ የመድሃኒቶ ጤና ክብካቤ ቁጥጥርና አስተዳደር ባለስልጣን ገለፀ፡፡

ባለስልጣኑ አለም አቀፉን የፀረ አደንዛዥ እጽ ቀንን ምክንያት በማድረግ አደገኛ መድሃኒቶችና እጾች አጠቃቀም እንዲሁም ህገ ወጥ ዝውውርን በተመለከተ  ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡

በባለስልጣኑ የህግ ጉዳዮች ዳይሬክተር አብረሀት ግደይ  ወጣቱ ትውልድ ከእነዚህ ጎጂ ሱሶች በመጠበቅ ረገድ ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ  እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ህገ ወጥ የአደንዛዥ እጽ አዘዋዋሪዎችን ለህግ በማቅረብ በኩል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

ሪፖርተር:-አማረ ተመስገን