ዛምቢያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች

ሰኔ 29፣2009

ዛምቢያ የአስቸኳይ ጊዜ ማወጇን የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኤድጋር ሉንጉ አስታወቁ።

ፕሬዝዳንቱ እንደገለጹት አገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀችው ካለፈው ሚያዝያ ጀምሮ በዋና ከተማዋ ሉሳካ የሚገኘውን ዋና ባንክ ጨምሮ አምስት  ሺህ ሱቆችን የያዘ ገበያ ለማጥቃት የተቀሰቀሰውን  ብጥብጥ ለማስቆም ነው፡፡

የአገሪቱ ቴሌቨዥን እንደገለፀው ፕሬዚዳንት ኤድጋር ሉንጉ በአገሪቱ  ህገ መንግስት አንቀጽ 31 መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማፀደቅ ነገ ለፓርላማ ያቀርባሉ፡፡

ፖርላማውም እስከ 90 ቀናት ሊቆይ የሚችልና እንደ አስፈላጊነቱ ሊራዘም የሚችል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊደነግግ ይችላል ተብሏል፡፡    

በአገሪቱ ከሚያዚያ አስከ ሰኔ ወር በተቀሰቀሰው ብጥብጥ ሳብያ በሉሳካ ካምፓላ  120 የገበያ አዳራሾች መቃጠላቸው ተገልጿል፡፡

ምንጭ:-ዎርልድቡሌቲን