ግብፅ የአስችኳይ ጊዜ አዋጁን ለ3 ወራት አራዘመች

ሰኔ 30፤ 2009

የግብፅ መንግስት በሀገሪቱ የሚከሰተውን የሽብር ተግባር ለመከላከል የተገበረውን የአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ ሶስት ወራት ማራዘሙን አስታወቀ፡፡

ፓርላማው አዋጁ እንዲራዘም የፈቀደው መንግስት የያዘውን የፀረ-ሽብር ዘመቻ ሰፊ ጊዜ ለመስጠት ነው ተብሏል፡፡

በግብፅ በሁለት የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ላይ በደረሰ የሽብር ጥቃት የ45 ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎም ግብፅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተግባራዊ አድርጋለች፡፡

ይሁን እንጂ ሀገሪቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ሆናም የሽብር ጥቃት እንደማያጣት ሰሞኑን በጦር መኮነኖች መኪና ላይ በተጠመደ ቦምብ የፀጥታ አካላት መገደላቸው ማሳያ ሆኗል፡፡

ግብፅ አይ ኤስ የሽብር ቡድኖች አሁንም ስጋቷ ሆኖ ቀጥለዋል፡፡

ምንጭ፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር