የኮምበልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተመረቀ

ሐምሌ 01፤2009

የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢንዱስትሪ  ፓርኮች ግንባታ ለአገሪቱ ኢንዱስትሪ ሽግግር ከፍተኛ ሚና አላቸው ብለዋል።

በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሼዶች ግንባታ ብቻውን በቂ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ በቀጣይ ባለሀብቶችን አስቀድመን ወደ ስራ ማስገባት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በሼዶቹ ባለሀብቶች ገብተው ስራ ሲጀምሩ የስራ አጥነት ችግሩ ይቃለላል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ተጨማሪ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለማልማትም እርሾ ይሆናሉ ብለዋል።

ባርኮች በሚገነቡባቸው ስፍራዎች የስራና መረጋጋት ጉዳይ ወሳኝ መሆኑ የገለጹት ጠቅላይ ሚንስትሩ የአከባቢው ሕብረተሰብ ባለሀብቶችን በማበረታታትና ሰላምና መረጋጋት እንዲስፍን የድርሻው እንዲወጣ ጠይቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በሀገሪቱ እየተገነቡ ያሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ውጤታማ እንዲሆኑ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡

የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተገነባው በቻይናው ሲቪል ኢንጂነሪንግ   ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ነው።