ጋና የመጀመሪያዋን ሳተላይት ወደ ህዋ አመጠቀች

ሐምሌ 01፣2009

ጋና የመጀመሪያዋን ሳተላይት ወደ ህዋ በተሳካ ሁኔታ አመጠቀች፡፡

በአገሪቱ ኦል ኔሽንስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተገነባች  ጋና ሳት-1 ሳተላይቷ  ከዓለም አቀፉ የህዋ ማዕከል መምጠቋ ተነገሯል፡፡

ሳታላይቷ ወደ ህዋ ከመጠቀች በአጭር ጊዜ ውስጥ ሲግናል ወደ ምድር መላክ መጀመሯ ተገልጿል።

50 ሺሀ የአሜሪካን ዶላር የወጣበት ሳታላይት የማምጠቅ ፕሮጀክቱ ከጃፓን የህዋ ሳይንስ ምርምር ኤጀንሲ ድጋፍ አግኝቷል ተብሏል፡፡

ሳተላይቷ የሀገሪቱን ወሰን ለመቃኘት፣ ካርታ ለማዘጋጀትና በህዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላትን አቅም ለማጠናከር ያግዛል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡