በሽታንና ድህነትን ለመከላከል ታዳጊ አገራት ከፍተኛ የመረጃ ትንተናን መጠቀም አለባቸው

ሃምሌ 4፤2009

የእድገት ማነቆዎችን ለመፍታት ከምርት እድገት ጀምሮ ተላላፊ በሽታዎችን ለመቆጣጠር ከፍተኛ የመረጃ ትንተናን መጠቀም በታዳጊ ሃገራት ዘንድ እየጨመረ መምጣቱን ባለሙያዎች ገለጹ፡፡

ፓዎል ሲዚያርቶ የቢግ ዳታ ፕሮግራም ሃላፊ እንደገለፁት በርካታ ታዳጊ ሃገራት የተለያዩ መረጃዎችን በመሰብሰብ  በማደራጀትና በመተንተን ድህነትን ለማጥፋት ሙከራዎችን እያደረጉ ይገኛሉ᎓᎓

ለምሳሌ ያህል ኬኒያና ህንድ የአየር ሁኔታን የተመለከቱ መረጃዎችን እንዲሁም የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ደግሞ እንደ ኢቦላ ያሉ ተላላፊ በሽታዎችን የሚመለከት መረጃዎችን በመሰብሰብ ሊከሰቱ የሚችሉትን ለውጦች ይከታተላሉ፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህ ታዳጊ ሃገራት ዘርፉ የሚፈልገውን መሰረተ ልማት ባለማሟላታቸው ምክንያት የቢግ ዳታ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዳልሆኑ ነው ባለሙያው ያብራራው፡፡

ምንጭ፡ ሮይተርስ