በአመራር ሰጪነት ሴቶች ከወንዶች እንደሚሻሉ በጥናት ተረጋገጠ

ሐምሌ 04፤2009

በስራ አመራርና በተቋማዊ ስነ ባህሪ በ3000 የስራ ኃላፊዎች ላይ በተደረገው ጥናት በተለይ በስራ አመራር በኩል ሴቶች ከወንዶች የተሻለ ብቃት እንዳላቸው ለማረጋጥ ተችሏል፡፡

ጥናቱ በተደረገባቸው መስፈርቶ ሁሉ ሴቶ ከአቻ ወንዶች የተሻሉ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡

ሴቶች በስራ ተነሳሽነት፣ ግልጽነት በተሞላው ግንኙነት፣ በፈጠራ ችሎታ፣ በሰላማዊ የስራ ግንኙነት፣ ድጋፍ ሰጪነት፣ ብልህነት በተሞላው አመራር እና የጠራ ግብ በማስቀመጥ ረገድ ከወንዶች ልቀው ተገኝተዋል፡፡

ይህም ሆኖ ወንዶች ከስራ ጋር በተያያዘ የሚፈጠር ጭንቀትን በመቋቋምና በመረጋጋት ከሴቶቹ ተሽለው ተገኝተዋል፡፡

በደንበኛ አያያዝና እንግዳ አቀባበል ሴቶች ሁልጊዜ ከወንዶች እንደሚሻሉም ጥናቱ አመላክቷል፡፡

በአሜሪካ ከ500 ጠንካራ ተቋማት ውስጥ የሴቶች አመራር 12 በመቶ ብቻ ነው፡፡

ይህንን እውነታ ያልተቀበሉ ድርጅቶች የአመራርነት ቦታቸውን ለሴቶ ክፍት ባለማድረጋቸው አነስተኛ አመራሮችን እቀጠሩ በምርታማነት ላይ ተፅዕኖ እየፈጠሩ ነው ተብሏል፡፡   

ምንጭ፡ ዘ ኢንዲንፔንደት